AMN- ጥቅምት 21/2017 ዓ.ም
2017 ዓ.ም ለኢትዮጵያ የማንሰራራት ዘመን ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ፡፡
6ኛው የህዝተወካዮች ምክር ቤት ብ 4ኛ ዓመት 3ኛ መደበኛ ስብሰባ እየተካሄደ ነው፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እየሰጡ ነው፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምላሻቸው ባለፈው ዓመት 8 ነጥብ 1 በመቶ የኢኮኖሚ እድገት መመዝገቡን አንስተዋል፡፡
በዚህ ዓመትም 8 ነጥብ 4 በመቶ እድገት እንደሚመዘገብ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) አስረድተዋል፡፡
የተመዘገበው የኢኮኖሚ እድግትም በተለያዩ የዓለም ተቋማት እውቅና ማግኘቱን አስረድተዋል፡፡ ይህም የሚታይና የሚጨበጥ እድገት እንደሆነ እና በዚህ ዓመት ያለፉት 3 ወራት እንቅስቃሴ ከተገመተው 8 ነጥብ 4 በመቶ በላይ እድገት ሊመዘገብ እንደሚችል አመላካች መሆኑን አንስተዋል፡፡
በሰለሞን በቀለ