ኢትዮጵያ ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስ፣ የአፍሪካ ኅብረት እና ኢጋድ ጋር በመሆን ለሱዳን ሕዝብ የሰብዓዊ ድጋፍ ከፍተኛ ኮንፈረንስ በጋራ በማዘጋጀቷ ደስታ ይሰማታል። እንደ ቅርብ ጎረቤት እና እህት ሀገር ኢትዮጵያ በዚህ የፈተና ጊዜ ከሱዳን ሕዝብ ጋር በአጋርነት ትቆማለች። ሁለቱ ሀገሮቻችን በጥልቅ የተሳሰሩ በትውልዶች የጋራ ትግል፣ የጋራ ምኞት እና ባሕላዊ ቁርኝት የተጋመዱ ናቸው።