23ኛው የአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ የሚኒስትሮች ስብሰባ በአዲስ አበባ ይካሄዳል

You are currently viewing 23ኛው የአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ የሚኒስትሮች ስብሰባ በአዲስ አበባ ይካሄዳል

AMN-ጥቅምት 19/2017 ዓ.ም

23ኛው የአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ የሚኒስትሮች ስብሰባ በመጪው የካቲት ወር በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ የተመራው ከፍተኛ የልኡካን ቡድን ከአለምአቀፉ የገንዘብ ድርጅት እና የአለም ባንክ 2024 አመታዊ ስብሰባ ጎን ለጎን በተካሄደው በ22ኛው የአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ የሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ተሳትፏል።

በስብሰባው የአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቴቭ እስከ አሁን ያስመዘገባቸው ስኬቶች እና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ምክክር እንደሚደረግ ተመላክቷል።

የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አመራር ሰጪነት ኢትዮጵያ እያከናወነች የምትገኘውን የኢኮኖሚ ማሻሻያ አስመልክቶ ማብራሪያ መስጠታቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review