የሲኖትራክ ኩባኒያ የቴክኒክ ችግር ያለባቸውን የሲኖትራክ መኪኖች በተለይም ገልባጮችን ስታንዳርዳቸውን ለማሟላት ቃል በገባዉ መሠረት ማስተካከል መጀመሩን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ባረኦ ሀሰን የሲኖትራክ ኩባኒያ የቴክኒክ ቡድን በኢትዮጵያ እያደረገ ያለዉን የስራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል።
ኩባንያዉ ፍሬናቸው አካባቢ ባለዉ የቴክኒክ ችግር ምክነያት የትራፊክ አደጋ ሲያደርሱ የነበሩ እና ይህም በጥናት የተደረሰባቸውን ችግሮች ለማስተካከል በተስማማዉ መሠረት የማስተካከል ስራ መጀመሩን ሚኒስትር ዴኤታዉ በስፍራዉ በመገኘት አረጋግጠዋል።
ምርቶቹ በዋናነት ያላሟሏቸውም የውስጥ እና ውጪ 360 ድግሪ የሚያሳዩ ካሜራዎች፣ የፍሬን ጥንካሬ ፣ ከተፈቀደ ክብደት በላይ ሲጫን የሚያሳውቅ ማንቂያ፣ ጭነት በየቦታው እንዳይፈስ የሚከላከል የጣሪያ ክዳን እና ሌሎች ክፍሎችን መመልከታቸዉን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ በላከዉ መረጃ አስታዉቋል።