2ኛው የምስራቅ አፍሪካ የጥበባትና ባህል ፌስቲቫል የማጠቃለያ መርሀ ግብር እየተካሄደ ነው።
የጥበባትና ባህል ፌስቲቫል አካል የሆነው የፋሽን ሾው፣ የስዕል አውደ ርዕይ፣ ሀገራዊ ባህላዊ ጭፈራዎች፣ የሰርከስ ትሪኢት፣ ኢግዚብሽንን ጨምሮ ልዩ ልዩ ዝግጅቶች በምስራቅ አፍሪካ ተሳታፊዎች እየቀረቡ ይገኛል።
በዝግጅቱም የባህል ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ፣ ሚኒስትር ዴኤታ ነፊሳ አልማህዲ፣ የምስራቅ አፍሪካ የባህልና ስፖርት ሚኒስትሮች ፣ የኪነጥበብ ባለሙያዎች እንዲሁም ክልል እና የከተማ አስተዳደሮች መገኘታቸውን ከባህል ስፖርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።