የካቲት 13/2017 ዓ.ም
በመድረኩ ብልፅግና ፓርቲ በሁለተኛው መደበኛ ጉባኤ ያስቀመጣቸውን አቅጣጫዎች በላቀ አፈፃፀም ለመተግበር የህብረተሰቡን ተሳትፎ ማሳደግ እንደሚገባ ተመላክቷል።
በውይይት መድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ የንግድ ቢሮ ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሀቢባ ሲራጅ፣ የአራዳ ክፍለ ከተማ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጌታሁን አበራ እና የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች እየተሳተፉ ይገኛል።
በውይይት መድረኩ የ2ኛው የብልጽግና ፓርቲ መደበኛ ጉባኤ ውሳኔዎች እና አቅጣጫዎች የተመለከተ ጽሁፍ በወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ አማካኝነት ቀርቧል።
በመድረኩ የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጌታሁን አበራ፣ ብልፅግና ፓርቲ በሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ያስቀመጣቸውን አቅጣጫዎች በላቀ አፈፃፀም ለመተግበር የህብረተሰቡን ተሳትፎ ማሳደግ እንደሚገባ አመላክተዋል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች በቀረቡ ሰነዶች ላይ ጥያቄ እና አስተያየት እየሰጡ ይገኛል።
በመሀመድኑር አሊ