3 ሺህ 285 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

You are currently viewing 3 ሺህ 285 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

AMN- ሚያዝያ 13/2017 ዓ.ም

በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 3 ሺህ 285 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

በሳምንቱ ውስጥ በተደረገ 9 ዙር በረራ የተመለሱት 2 ሺህ 747 ወንዶች እና 508 ሴቶች፣ 30 ጨቅላ ህፃናት ሲሆኑ፣ ከተመላሾች መካከል 159 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል።

በ4ኛው ዙር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ 50 ሺህ ዜጎችን ለመመለስ ታቅዶ መጋቢት 3 በይፋ በተጀመረው እንቅስቃሴ፣ እስካሁን 18 ሺህ 969 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ መቻሉን ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሚመለከታቸው ባለድርሻና አጋር አካላት ጋር በመቀናጀት ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራም እየሰራ እንደሚገኝ አመላክቷል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review