38ኛውን አፍሪካ ኀብረት የመሪዎች ጉባኤ በላቀ ደረጃ ለማስተናገድ አስፈላጊ ዝግጅት ተደርጓል-አምባሳደር ብርቱካን አያኖ

You are currently viewing 38ኛውን አፍሪካ ኀብረት የመሪዎች ጉባኤ በላቀ ደረጃ ለማስተናገድ አስፈላጊ ዝግጅት ተደርጓል-አምባሳደር ብርቱካን አያኖ

AMN – ጥር 16/2017 ዓ.ም

ለመጪው የአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ የሚሰማሩ ለቪ.አይ.ፒ. አጃቢዎች እና አሽከርካሪዎች ሲወስዱ የነበረውን ስልጠና አጠናቀው ተመርቀዋል።

በፌደራል ፖሊስ ዋና መስሪያቤት በተከናወነው ስነ ስርዓት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ባደረጉት ንግግር ፣ ጉባኤውን በተሳካ ሁኔታ ለማካሄድ አስፈላጊው ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል።

ስልጠናውን የወሰዱ የቪ.አይ.ፒ. አሽከርካሪዎች እና አጃቢዎች የሚሰጣቸውን ስምሪት ሙያዊ ደረጃውን በጠበቀ መስተንግዶ እና በላቀ አገልግሎት መፈፀም እንዳለባቸው ሚኒስትር ዴኤታዋ አሳስበዋል።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል እንዳሉት ፥ ጉባኤውን በአስተማማኝ ፀጥታ እና ደህንነት ለማከናወን የሚያስችል ካለፉት ጊዜያት የበለጠ ዝግጅት ተደርጓል።

ስልጠናው የንድፈ ሀሳብ እና የተግባር ተኮር ስልጠና እንደነበረ ገልፀው በቅንጅት በመስራት ለጉባኤው ስኬት የተጣለባቸውን ሃላፊነት እንዲወጡ ኮሚሽነር ደመላሽ ጥሪ ማቅረባቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review