AMN – የካቲት 9/2017 ዓ.ም
38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በኢትዮጵያ ብሎም በአዲስ አበባ ያለውን ፈጣን ለውጥ ጉባኤተኞቹ የተገነዘቡበት እንደሆነ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ፡፡
ከጉባኤው ጋር በተያያዘ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዲኤታው ተስፋሁን ጎበዛይ መግለጫ ሰጥተዋል
በመግለጫውም በ38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ የሚገኙ የተለያዩ ሀገራት መሪዎች እና እንግዶች ጉባኤውን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ያላቸውን ትርፍ ጊዜ አዲስ አበባን እዲጎበኙ መደረጉን አመለክተዋል ፡፡

በጉብኝቱም ጉባኤተኞቹ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ተሞክሮ መሆን የሚችል የልማት ስራ መመልከታቸውን ተናግረዋል፡፡
በአፍሪካ ውስጥ ያለውን የሰላም እና የደህነት ስጋት እና ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የአፍሪካዊያንን ችግሮች በአፍሪካዊያን መፍታት የሚለውን መርህ በመከተል የአፍሪካ ሕብረት የደህንነት እና የፀጥታ ምክር ቤት በተጠናከረ መልኩ ስራውን እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በጉባኤው አሁን ያለውን እና ወደ ፊትም ሊመጡ የሚችሉ ክስተቶች አፍሪካ መቋቋም የምትችልበት ስርዓት ለመዘርጋት እና አፍሪካ ሕብረት የተሻለ ቁመና እንዲይዝ ለማድረግ ያለመ ምክረ ሀሳብ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጓል ብለዋል ሚኒስትር ዴኤታው ፡፡
በጉባኤው የአፍሪካ የበሽታዎች መከላከያና መቆጣጠሪያ ማዕከል ( CDC) ከተቋቋመ በአጭር ጊዜ ስኬታማ እንደሆነም መነሳቱን ጠቅሰዋል፡፡
በህዝባችን ተሳትፎ የጉባኤው ሂደት ስኬታማ ሆኗል ያሉት ፣ ሚኒስትር ዴኤታው አፍሪካ በጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ ውክልና እንዲኖራት ለማድረግ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒ ዮ ጉተሬዝ የገቡትን ቃል የሚደግፍ ውይይትም መካሄዱን ጠቁመዋል ፡፡
ዳንኤል መላኩ




All reactions:
91Us Man Mohammed and 90 others