38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ተጠናቀቀ።

You are currently viewing 38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ተጠናቀቀ።

AMN- የካቲት 09/2017 ዓ.ም

38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ የማካካሻ ፍትህ ለአፍሪካውያን እና ለዘርዓ-አፍሪካውያን ማስገኘት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቀቀ።

ጉባኤው ባርነት፣ አስገድዶ ወደ ሀገር መመለስ (ዲፖርቴሽን) እና ቅኝ ገዥነት በአፍሪካውያን ላይ የተፈጸመ የዘር ማጥፋት ተግባር ሆኖ እንዲበየን በቶጎ የቀረበውን ሀሳብም አጽድቋል።

ውሳኔው አፍሪካውያንና ዘርዓ-አፍሪካውያን ከባርነት፣ አስገድዶ ወደ ሀገር መመለስ (ዲፖርቴሽን) እና ቅኝ ገዥነት ጋር በተያያዙ የተፈጸሙባቸው ወንጀሎች እውቅና እንዲያገኙ እና እንዲካሱም የሚያደርግ ነው ተብሏል።

በሰብስቤ ባዩ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review