38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ እና 46ኛው የሚኒስትሮች ስብሰባ ስኬታማ እንዲሆን በቂ ዝግጅት እየተደረገ ነው፡- ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል

You are currently viewing 38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ እና 46ኛው የሚኒስትሮች ስብሰባ ስኬታማ እንዲሆን በቂ ዝግጅት እየተደረገ ነው፡- ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል

AMN – ጥር 16/2017 ዓ.ም

38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ እና 46ኛው የሚኒስትሮች ስብሰባ ስኬታማ እንዲሆን በቂ ዝግጅት እየተደረገ ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ገለጹ፡፡

በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የሰለጠኑ የVIP ፕሮቶኮል አጃቢዎች እና የአሽከርካሪዎች ምረቃ ሥነ-ሥርዓት ተካሂዷል።

ጉባኤው የተሳካ እንዲሆን ተቋሙ የታጠቃቸው ድሮኖችና ሌሎች ዘመኑን የሚመጥኑ ቴክኖሎጂዎች ሥራ ላይ እንደሚውሉ አንስተው የሰው ኃይሉን በሀገር ውስጥ፤ በቻይና፤ በተባበሩት ዐረብ ኢሚሬት ዱባይ በማስልጠን እና የፀጥታ ሥራውን በማዘመን ከፍተኛ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በመርሀግብሩ ላይ ገልፀዋል።

በስልጠና ያገኛችሁትን ዕውቀትና ክህሎት በተግባር ላይ በማዋል፣ በጥብቅ ዲሲፕሊንና በቅንጅት በመስራት አምባሳደር ሆናችሁ የሀገራችንን ገፅታ የበለጠ ከፍ በማድረግ የሕብረቱ ጉባኤ የተሳካ እንዲሆን መሥራት ይጠበቅባችኋል በማለት ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ለተመራቂዎች የሥራ መመሪያ ሰጥተዋል።

በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ስልጠና የወሰዱት የVIP ፕሮቶኮል አጃቢዎች እና አሽከርካሪዎች ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከብሔራዊ ቤተመንግስት፣ ከባህልና ቱሪዝም፣ ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ፣ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ ከአዲስ አበባ ፖሊስ፣ የራይድ ትራንስፖርት እና የመኪና አከራይ ድርጅቶችን ጨምሮ ከ55 ተቋማት የተውጣጡ መሆናቸውን ከኮሚሽኑ ተገኘው መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review