38ኛውን የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤን ከፍ ባለ ሁኔታ ለማስተናገድ የመዲናችንን ቅድመ ዝግጅት ገምግመናል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN-ታህሳስ 14/2017 ዓ.ም

ዛሬ ማለዳ 38ኛውን የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤን ከፍ ባለ ሁኔታ ለማስተናገድ የመዲናችንን ቅድመ ዝግጅት ገምግመናል።

የአፍሪካዊያንና የዓለም የዲፕሎማቲክ ማዕከል፤ የህብረብሄዊነት አርማ የሆነችዉ ከተማችን አዲስ አበባ ይህንን ታሪካዊ ጉባኤ በደመቀ እና ባማረ መልኩ ለማስተናገድ ከወትሮ በተሻለ መልኩ እንግዶቿን ለመቀበል አስፈላጊውን ቅደመ ዝግጅት በማድረግ ላይ መሆንውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልፀዋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ የከተማችን ነዋሪዎችም እንግዶችን በተለመደው ኢትዮጵያዊ ጨዋነት እና እንገዳ ተቀባይነት ለመቀበል፣ በየአካባቢዉ ከወዲሁ ከተማችንን ውብ እና ፅዱ በማድረግ እንዲሁም በእንኳን ደህና መጣችሁልን መንፈስ ሃላፊነታችንን በመወጣት የሃገራችንን ስም እና ክብር ከፍ ለማድረግ ተባብረን እንስራ ብለዋል በመልዕክታቸው።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review