46ኛው የካፍ ጠቅላላ ጉባዔ ዛሬ ይካሄዳል

You are currently viewing 46ኛው የካፍ ጠቅላላ ጉባዔ ዛሬ ይካሄዳል

AMN- ጥቅምት 12/2017 ዓ.ም

46ኛው የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ጠቅላላ ጉባዔ ዛሬ በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

በጉባዔው ላይ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ሞትሴፔ እና የካፍ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት፣ የዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ እና የፊፋ ዋና ፀሐፊ ማትያስ ግራፍስትሮም፣ የካፍ አባል አገራት እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች እና የቀጣናዊ እግር ኳስ ማህበራት ፕሬዝዳንቶች እንዲሁም ሌሎች የስፖርቱ ባለድርሻ አካላት ይሳተፋሉ።

ጉባዔው በአፍሪካ እግር ኳስ ጉዳዮች ላይ በመምከር የተለያዩ ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል።

ኢትዮጵያ የካፍ ጠቅላላ ጉባዔን ስታስተናግድ የአሁኑ ለሁለተኛ ጊዜ ነው።

ከዚህ ቀደም እ.አ.አ በ2017 39ኛውን የአፍሪካ ጠቅላላ ጉባዔ አዘጋጅታ ነበር።

23 አባላት ያሉት የካፍ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባውን ትናንት ማድረጉ ይታወቃል።

የ46ኛው የካፍ ጠቅላላ ጉባዔ አካል የሆነው የቀጣናዊ እግር ኳስ ማህበራት ስብስባ ትናንት እና ከትናንት በስቲያ መካሄዱን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review