AMN -ጥቅምት 1/2017 ዓ.ም
5ተኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር በሳይንስ ሙዚየም እየተካሄደ ነው፡፡
“የቁልፍ መሰረተ-ልማት ደህንነት ለዲጂታል ሉዓላዊነት” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ በሚገኘው መርሐግብር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ፣ ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቤ ሳኖ፣ የኢትዮቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።