AMN- ጥቅምት 27/2017 ዓ.ም
ከ30 ሺ በላይ የስራ እድሎችን ለመፍጠር የሚያስችል 5ኛው ሀገር አቀፍ የስራ አዉደ ርእይ በሚኒልየም አዳራሽ ተጀምሯል።
መረሀግብሩን የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ከደረጃ የኢንፎርሜሽን ሶሊዉሽን ማህበራዊ ድርጅት እና ከማስተር ካርድ ፋዉንዴሽን ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው ተብሏል ።
ከ300 በላይ ቀጣሪ ድርጅቶች መሳተፋቸውን የስራ እና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰለሞን ሶካ ተናግረዋል ።
ይህ መርሀግብር የስራ አጥ ቁጥርን ከመቀነስ ባሻገር ሀገሪቱ በኢንዱስትሪ ዉስጥ የምትፈልገዉን የሰዉ ሀይል ለመሙላት አቅም የሚሆን ነዉ ብለዋል።
በተለያዩ ዩንቨርስቲዎች የስራ ምዝገባ የተካሄደ ሲሆን ይህ በሌሎች አከባቢዎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተገልጿል ።
አገረ አቀፍ የስራ አዉደ ርዕዩ እስከ ነገ ጥቅምት 28 የሚቆይ ነዉ፡፡
በሩዝሊን መሀመድ