550 ሺህ ኩንታል ዳፕ የአፈር ማዳበሪያ የጫነች መርከብ ወደብ ደረሰች

AMN – ታኅሣሥ 4/2017 ዓ.ም

ለ2017/18 የምርት ዘመን ከውጭ እየተጓጓዘ ከሚገኘው የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ 550 ሺህ ኩንታል ዳፕ የጫነች መርከብ ታኅሣሥ 3 ቀን 2017 ዓ.ም ምሽት ጂቡቲ ወደብ ደርሳለች።

በቅርብ ቀናት 2.4 ሚሊየን ኩንታል ዳፕ የጫኑ አራት መርከቦች ወደብ ይደርሳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም የኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን መረጃ አመላክቷል።

ለዘንድሮ የምርት ዘመን ከሚያስፈልገው የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ እስከአሁን ከ1 ሚሊየን ኩንታል በላይ ወደብ የደረሰ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥም 472 ሺህ 210 ኩንታል ወደ ሀገር ውስጥ መጓጓዙ ተገልጿል።

የግብርና ሚኒስቴር በየዓመቱ እያጠና በሚያቀርበው የሀገሪቱ የአፈር ማዳበሪያ ፍላጎት መሰረት የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢግሥኮ) ዓለም አቀፍ ጨረታ እያወጣ የማዳበሪያ ግዥ በመፈጸም ላይ እንደሚገኝም ነው ያመላከተው።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review