የዕደ-ጥበብ ፈጠራ ምርቶች አውደ-ርዕይ ተከፈተ

You are currently viewing የዕደ-ጥበብ ፈጠራ ምርቶች አውደ-ርዕይ ተከፈተ

AMN- ጳጉሜን 2/2018 ዓ.ም

መጪውን አዲስ አመት ምክንያት በማድረግ የዕደ-ጥበብ ፈጠራ ምርቶች አውደ-ርዕይ ተከፍቷል፡፡

“የሀገሬን የዕደ-ጥበብ ምርት አስተዋውቃለሁ፤ እጠብቃለሁ እጠቀማለሁ” በሚል መሪ ሀሳብ በጣይቱ የባህል የትምህርት ማዕከል ነው አውደ-ርዕዩ የተከፈተው፡፡

በአውደ-ርዕዩ ባህላዊ አልባሳት፣ የቤት ማስዋቢያ ቁሳቁሶች፣ የቆዳ፣ የእንጨት እና የሸክላ ውጤቶች ለሽያጭ ቀርበዋል።

አውደ – ርዕዩን የከፈቱት የአዲስ አበባ ባህል እና ኪነ-ጥበባት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ እና የባህል ዘርፍ ኃላፊው አዲሱ ሻንቆ (ዶ/ር) ከተማ አስተዳደሩ ለዕደ-ጥበብ በተሰጠው ትኩረት የማንሰራራት ጊዜ ላይ መድረሱን ገልፀዋል።

እንደ ሀገር የሀገር ውስጥ ምርቶችን መጠቀም ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው ያሉት ምክትል ቢሮ ኃላፊው ፤ ህብረተሰቡ በሀገር ውስጥ ምርት የመጠቀም ባህልን እንዲያሳድግም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በአውደ- ርዕዩ ከ70 በላይ የዕደ-ጥበብ አምራቾች የተሳተፉ ሲሆን ምርቶቻቸውን ከንፁህ ጥሬ ዕቃዎች ማምረታቸውንና ከመደበኛው የገበያ ዋጋ በቅናሽ ማቅረባቸውን ተናግረዋል።

በጣይቱ የባህል እና የትምህርት ማዕከል እየተካሄደ ያለው ይህ አውደ-ርዕይ እስከ ጷጉሜን 5 እንደሚቆይም ተገልጿል።

በበኃይሉ አያሌው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review