አዲሱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተቋማት አደረጃጀት

You are currently viewing አዲሱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተቋማት አደረጃጀት

AMN- መስከረም 20/2019 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ባካሄደው የመንግስት ምስረታና 4ኛ ዙር የመክፈቻ ጉባኤ፣ የከተማዋን አስተዳደር መዋቅር የሚቀይርና አዳዲስ ቢሮዎችን የሚያቋቁም ረቂቅ አዋጅ አጽድቋል።

በዚህም መሠረት የተደረጉ መዋቅራዊ ለውጦች፦

• የሥራና ክህሎት ቢሮ፦ ለሁለት በመክፈል የሠራተኛና ሥራ ዕድል ፈጠራ ቢሮ እና የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ቢሮ ተብሎ እንዲደራጅ ተደርጓል።

• ባህልና ቱሪዝም፦ የባህልና ኪነ-ጥበብ ቢሮ እና የቱሪዝም ኮሚሽን በመዋሃድ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሆኗል።

• ትራንስፖርት፦ የትራፊክ ማኔጅመንት ባለሥልጣን ታጥፎ ተግባሩ ለትራንስፖርት ቢሮ፣ ለመንገዶች ባለሥልጣን እና ለአዲሱ ትራንስፖርት ማኔጅመንት ማዕከል ተከፋፍሏል።

• ኢንቨስትመንት፦ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች አደረጃጀት ባለሥልጣን በኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ተተክቷል።

• የተሰረዙ ተቋማት፦ የመሥሪያ ቦታዎች ልማት አስተዳደር ኤጀንሲ፣ የምግብ ኤጀንሲ፣ የአዲስ አበባ ሥራዎች አካዳሚ እና የህዳሴ ግድብ አስተባባሪ ጽሕፈት ቤት ታጥፈው ተግባራቸው ለሌሎች አካላት ተላልፏል።

•

አዲሱ አዋጅ 7 ክፍሎች እና 98 አንቀጾች ያሉት ሲሆን፣ ቀልጣፋ አሠራር በመዘርጋት የከተማዋን ዕድገት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተመላክቷል።

በወርቅነህ አቢዮ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review