የኢፌዲሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት 7ኛው የፓርላማ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባዔውን ዛሬ ያካሄዳል

AMN መስከረም 25/ 2019 ዓ.ም

የኢፌዴሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት የ7ኛው የፓርላማ ዘመን 1ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ 1ኛ መደበኛ ጉባዔውን መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም ያካሄዳል።

በቅርቡ የተካሄደውን ጠቅላላ ምርጫ ተከትሎ፣ በኢፌዴሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 61 ንዑስ አንቀጽ 1 እስከ 3 በተደነገገው መሠረት የፌዴሬሽን ምክር ቤት በክልል ምክር ቤቶች የሚወከሉ የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ተወካዮችን በመቀበል እንደሚዋቀር የፌዴሬሽን ምክር ቤት የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ተረፈ በዳዳ አስታውቀዋል።

ዳይሬክተሩ እንዳመለከቱት፣ መስከረም 24 ቀን 2019 ዓ.ም ለምክር ቤቱ አባላት ስለ ምክር ቤቱ አሠራር የሚያስረዳ ገለጻ መደረጉን አስታውሰዋል።

እንዲሁም አቶ ተረፈ እንደገለፁት በጉባዔው ወቅትም በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 62(11) እና በተሻሻለው የፌዴሬሽን ምክር ቤት አዋጅ ቁጥር 1261/2013 መሠረት፦የምክር ቤቱ አፈ-ጉባዔና ምክትል አፈ-ጉባዔ ምርጫ እንደሚካሄድ፤ የቋሚ ኮሚቴዎች አባላት እንደሚመረጡ እና በሕገ-መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ የሚወክሉ አባላት እንደሚሰየሙ መገለጹን የምክር ቤቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review