ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ

You are currently viewing ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ

AMN- መስከረም 25/2019 ዓ.ም

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት፤ ለዚህ ያበቃን ፈጣሪያችንን እናመሠግናለን ብለዋል፡፡

መላው ሰላምና ልማት ወዳድ ኢትዮጵያውያን ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ፤እንኳን ደስ አለን ሲሉም ገልጸዋል፡፡

ጀግናው፣ ሀገር ወዳድና የኢትዮጵያ ስጦታ ጠቅላይ ሚኒስትራችን መልካም የስራ ዘመን በማለት ባለፉት ዓመታት ሀገራችንን ከገጠማት ዘርፈ ብዙ ውጣ ውረድ ታድገን፣ በተግባር ባረጋገጥነው የማይበገር ጽናት እና ሌት ተቀን ባከናወንናቸው ጠንካራ የልማት ሥራዎች የሕዝባችንን አመኔታና ድምፅ በማግኘት በድጋሚ በሕዝብ ይሁንታና ድምፅ ጠንካራ የመደመር መንግሥት ለመመሥረት ችለናል ብለዋል፡፡

ለኢትዮጵያችን ዳግም ማንሰራራት አርአያ የሆኑን በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መሪነት ለሀገር ሉዓላዊነት፣ ለፍትሐዊነትና ለዜጎች ሁለንተናዊ ብልጽግና በፅናት እንቁም፤ እንተባበር ሲሉም መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

ትናንት ፈተናዎችን በብቃት ተሻግረናል፤ በተግባር የተፈተነው አቅማችንና የተስፋ አድማሳችን እጅግ የገዘፈ ነውም ብለዋል።

ኢትዮጵያችን በእርግጠኝነት የጀመረችውን የብልፅግና ጉዞ ታሳካለች፤ በመላው ኢትዮጵያውያን ጽኑ ትብብር፣ የጋራ ርብርብ፣ ወንድማማችነትና የማይበጠስ አንድነት የታላቅነት ጉዟችን በእርግጥም ከጫፍ ይደርሳልም ነው ያሉት፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review