ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ዳግም መመረጣቸው በራዕያቸው ላይ የተጣለ እምነት ማሳያ ነው – ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ

AMN- መስከረም 26/2019 ዓ.ም

የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ኢትዮጵያን ለሁለተኛ የሥራ ዘመን ለመምራት ዳግም በመመረጣቸው የተሰማቸውን ደስታ በመግለጽ የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላለፉ።

ፕሬዚዳንት ሩቶ ባስተላለፉት የመልካም ምኞት መልዕክት ፣ በኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተሰጣቸው አዲሱ ይሁንታ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባላቸው ሀገራዊ ራዕይና የሥራ አመራር ብቃት ላይ የተጣለ ትልቅ እምነት ማሳያ ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ የያዘችውን የሀገራዊ ትራንስፎርሜሽን አጀንዳ እና የልማት ግቦች ለማሳካት በሚደረገው ጉዞ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ስኬታማ አመራር መስጠታቸውን እንዲቀጥሉ የመልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

ኬንያ የሁለቱን ሀገራት የጋራ ጥቅሞች ለማስከበር ፣ የሁለቱን አገራት ሕዝቦች ፣ የምሥራቅ አፍሪካ ቀጠናን እንዲሁም የዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ የጋራ ዕድገትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከኢትዮጵያ ጋር በቅርበትና በትብብር መስራቷን አጠናክራ እንደምትቀጥል ፕሬዚዳንቱ አረጋግጠዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review