AMN- የካቲት 20/2017 ዓ.ም
ለ2017/18 የምርት ዘመን ግብዓት የሚሆን 59 ሺህ 968.1 ሜትሪክ ቶን ማዳበሪያ የጫነ መርከብ ጅቡቲ ወደብ ደርሶ በማራገፍ ላይ እንደሚገኝ ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ለ2017/18 የምርት ዘመን ለማቅረብ ከታቀደው 24 ሚሊየን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ ከ600 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ መጓጓዙ ይታወቃል፡፡
ከ1.7 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን በላይ የአፈር ማዳበሪያ በ13 መርከቦች ተጭኖ ጅቡቲ ወደብ መድረሱንም አያይዞ ገልጿል።
ወደ ሀገር ውስጥ ከተጓጓዘው 632 ሺህ 965.2 ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ 95 ሺህ 340 ሜትሪክ ቶን የተጓጓዘው በአትዮ ጅቡቲ ምድር በባቡር መሆኑም ተመላክቷል፡፡
ቀሪው 537 ሺህ 625.2 ሜትሪክ ቶን የተጓጓዘው በድንበር ተሻጋሪ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎች መሆኑን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡