በአዲስ አበባ በህብረተሰብ ተሳትፎ የሚከናወኑ የበጎ ፈቃድ ሥራዎች ውጤታማ መሆናቸው ተገለጸ

You are currently viewing በአዲስ አበባ በህብረተሰብ ተሳትፎ የሚከናወኑ የበጎ ፈቃድ ሥራዎች ውጤታማ መሆናቸው ተገለጸ

AMN – ጥቅምት 17/2019 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ ሕብረተሰቡን በማሳተፍ የሚሠሩ የበጎ ፈቃድ ሥራዎች ውጤታማ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ሕብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን አስታወቀ።

ኮሚሽኑ በሕብረተሰብ ተሳትፎ የሚያስገነባቸውን የአካባቢ መሠረተ ልማት ሥራዎች በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አስጀምሯል።

የአካባቢው ነዋሪዎች ከዚህ በፊት የነበረው የውስጥ ለውስጥ መንገድ ለመንቀሳቀስ አስቸጋሪ እንደነበር በማስታወስ፣ የዚህ ግንባታ መጀመር በእጅጉ እንደአስደሰታቸው ለኤ ኤም ኤን ገልጸዋል።

መርሐ ግብሩን ያስጀመሩት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሕብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባባሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር ወ/ት ጽዮን ደረጀ፤ ከተማዋን ለነዋሪዎቿ ምቹና ተመራጭ ለማድረግ፣ በተለይም በሕብረተሰብ ተሳትፎ የተሠሩ ሥራዎች ሕብረተሰቡን ተጠቃሚ እያደረጉ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ዛሬ የተጀመረው የውስጥ ለውስጥ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክትም መንግሥትና የበጎ ፈቃድ ባለሀብቶች ከሕብረተሰቡ ጋር በጋራ ሲቀናጁ ማኅበራዊ ችግሮችን በዘላቂነት መፍታት እንደሚቻል ተጨባጭ ማሳያ ነው ብለዋል። በመሆኑም በመንገድ መሠረተ ልማት ሥራው ላይ የሕብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

ኮሚሽነር ፅዮን በ2018 በጀት ዓመት የተቀናጁ ሞዴል ብሎኮችን ለማስፋፋት የተሠራው ሥራ ውጤታማ እንደነበር ጠቅሰው፣ በያዝነው በጀት ዓመትም የተገኘውን ልምድ በመቅሰም የተቀናጁ ሞዴል ብሎኮችን አጠናክሮ ለመቀጠል እንደሚሠራ ተናግረዋል።

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አሕመድ ሐሰን በበኩላቸው፣ በሕብረተሰብ ተሳትፎና በመንግሥት የተተገበሩ ሥራዎች የብዙዎችን የኑሮ ሸክም ከማቅለል ባሻገር እርስ በእርስ የመደጋጋፍ እሴትን በማሳደግ ለሀገራዊ አንድነት መጠናከር የላቀ ፋይዳ ማበርከታቸውን ገልጸዋል።

በመሀመድኑር ዓሊ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review