በሳዑዲ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 364 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

You are currently viewing በሳዑዲ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 364 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

AMN-ጥቅምት 23/2019 ዓ.ም

በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 364 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

በሳምንቱ ውስጥ በተደረገ 6 ዙር በረራ የተመለሱት 1 ሺህ 360 ወንዶች፣ 4 ሴቶች ሲሆኑ ከተመላሾች መካከል 18 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል።

ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራም እየተሰራ ይገኛል፡፡

መስከረም 5 ቀን 2018 ዓ.ም በተጀመረው ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ እስካሁን ከ112 ሺህ 500 በላይ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ መቻሉን ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review