AMN-ጥር 22/2017 ዓ.ም
በአሜሪካን 60 የሀገር ውስጥ መንገደኞችን እና አራት የበረራ ሰራተኞችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ የመንገደኞች አውሮፕላን ፖቶማክ የተባለ ወንዝ አቅራቢያ ከጦር ሂሊኮፕተር ጋር አየር ላይ መጋጨቱ ተነግሯል።
ሄሊኮፕተሩ ሦስት ወታደሮችን ጭኖ እንደነበር ተገልጿል፡፡
አደጋውን ተከትሎ 300 የሚሆኑ የህይወት አድን ጀልባዎች እና ጠላቂዎች በፍለጋ ላይ ይገኛሉ፡፡
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሠራተኞቹን ህይወት አድን ተግባር ማድነቃቸውን የቢቢሲ ዘገባ አመልክቷል፡፡