6ኛው የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታ የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች እና የዉድድሩ ተሳታፊዎች በተገኙበት በጅማ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም እየተካሄደ ነው፡፡
ከዘጠኝ አመታት ቆይታ በኋላ እየተከናወነ የሚገኘው 6ኛው የመላው ኢትዮጵያዊ ጨዋታ ከ12 ክልሎችና 2 ከተማ አስተዳድሮች በተወጣጡ ስፖርተኞች እንዲሁም የጅማ ከተማ ነዋሪዎች በተገኙበት የመክፈቻ ፕሮግራም እየተከናወነ ይገኛል።
ደማቅ ባለ ሁኔታ እየተካሔደ በሚገኘው የመክፈቻ ፕሮግራም ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ፤ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አወሉ አብዲን ጨምሮ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮችና ሌሎች አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
ከሰዓት በኋላ የተለያዩ ስፖርታዊ ውድድሮች የሚከናወኑ ይሆናል።
በአንዱዓለም ስማቸው