72ኛዉን የቦረና አባ ገዳ ባሊ ርክክብን በማስመልከት የተካሄደው የብስክሌት ውድድር ተጠናቀቀ

You are currently viewing 72ኛዉን የቦረና አባ ገዳ ባሊ ርክክብን በማስመልከት የተካሄደው የብስክሌት ውድድር ተጠናቀቀ

AMN – የካቲት 28/2017 ዓ.ም

72ኛዉን የቦረና አባ ገዳ ባሊ ርክክብን በማስመልከት በብሄራዊ ቡድን ተወዳዳሪዎች መካከል የተካሄደው የ100 ኪሎ ሜትር የብስክሌት ውድድር ተጠናቋል፡፡

ዉድድሩን በቀዳሚነት ያጠናቀቀዉ ከብሄራዊ ቡድን ፊሊሞን ዘራብሩክ ሲሆን፣ ተመስገን መብራተ ከመቀሌ ሰባ አንደርታ 2ኛ፣ እንዲሁም ኪያ ጀማል ከብሄራዊ ቡድን በ3ኛነት አጠናቀዋል።

ተወዳዳሪዎቹ፣ በዚህ ታሪካዊ ዉድድር ላይ በመሳተፍ የገዳ ሥረዓትን ስላስተዋወቅን ደስ ብሎናል ብለዋል።

በዉድድሩ ተሳትፈዉ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ለወጡ ተወዳዳሪዎች 50ሺ፣ 40ሺ እና 30 ሺ ብር የተሸለሙ ሲሆን ለሌሎች ተሳታፊዎችም የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።

በዉድድሩ 86 ስፖርተኞች ተሳትፈዋል።

በጫላ በረካ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review