72ኛዉን የቦረና አባ ገዳ ባሊ ርክክብን በማስመልከት የብስክሌት ውድድር እየተካሄደ ነው

You are currently viewing 72ኛዉን የቦረና አባ ገዳ ባሊ ርክክብን በማስመልከት የብስክሌት ውድድር እየተካሄደ ነው

AMN – የካቲት 28/2017 ዓ.ም

72ኛዉን የቦረና አባ ገዳ ባሊ ርክክብን በማስመልከት 100 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚሸፍን የብስክሌት ዉድድር በያቤሎ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

ይህ የብስክሌት ዉድድር ገዳ ቱር የተሰኘ ሲሆን የገዳ ቱሪዝምን ለማስተዋወቅ ታልሞ የተዘጋጀ ነዉ።

በዉድድሩ ከተለያዩ ክልሎች፣ ከተሞችና ክለቦች የተወጣጡ 110 ስፖርተኞች የሚወዳደሩ ሲሆን ከሩዋንዳ ኪጋሊ የመጡ ስፖርተኞችም ተሳትፈዋል።

በዉድድሩ ከ1ኛ እስከ 10ኛ የሚወጡ አሸናፊዎች ሽልማት እንደሚበረከትላቸውም ተመላክቷል።

በጫላ በረካ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review