72ኛው የቦረና ኦሮሞ የገዳ ስልጣን (ባሊ) ርክክብ ስነ ስርዓት በማስመልከት የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው

You are currently viewing 72ኛው የቦረና ኦሮሞ የገዳ ስልጣን (ባሊ) ርክክብ ስነ ስርዓት በማስመልከት የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው

AMN – ጥር 16/2017 ዓ.ም

72ኛው የቦረና ኦሮሞ የገዳ ስልጣን (ባሊ) ርክክብ ስነ ስርዓት በማስመልከት የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው።

በውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ እንደገለጹት፣ መንግሥት ለባህል ዘርፍ በሰጠው ልዩ ትኩረት ባህላዊ እሴቶችን፣ ቋንቋ እና ኪነ-ጥበብን እንዲሁም የሃገሪቱን ቅርስ በማልማት ላይ ሰፊ ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡

በብሔር ብሔረሰቦች የሚገኘውን እምቅ ባህላዊ ዕውቀቶች ህጋዊ ሽፋን እንዲያገኙ ተደረጓልም ነው ያሉት፡፡

በተለይ በኦሮሚያ ክልል በባህላዊ ፍርድ ቤቶች ስኬቶች እየተመዘገቡ እንደሚገኝ በማውሳት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ መሰል ተሞክሮዎችን ወደ ሌሎች ክልሎች እንዲስፋፉ ድጋፍና ክትትል እንደሚያደረግ ተናግረዋል፡፡

መርሃግብሩ በተለያዩ ስነ-ስርዓቱን በሚወክሉ ባህላዊ ጨዋታዎችና ጭፈራዎች ደምቆ እየተካሄደ እንደሚገኝ የሚኒስቴሩ መረጃ ያሳያል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review