84ኛው የሳምቤ የአርበኞች ድል መታሰቢያ ነገ በኢሉአባቦር ዞን ይከበራል

You are currently viewing 84ኛው የሳምቤ የአርበኞች ድል መታሰቢያ ነገ በኢሉአባቦር ዞን ይከበራል

AMN ሚያዝያ 26/2017

የሳምቤ አርበኞች ፋሺስት ጣሊያንን ድል ያደረጉበት 84ኛው የመታሰቢያ ቀን ነገ በኢሉአባቦር ዞን ይከበራል።

በአሉን ምክንያት በማድረግ በመቱ ከተማ የፓናል ውይይት ተካሂዷል።

ሳምቤ በኦሮሚያ ክልል ኢሉአባቦር ዞን አሌ ወረዳ ጎሬ ከተማ አቅራቢያ የሚገኝ ስፍራ ነው።

ፋሺስት የጣሊያን ጦር በአድዋ ድል የደረሰበትን ሽንፈት ለመበቀል ወደ ጎሬ ከተማ ተንቀሳቅሶ እንደ ነበር ምሁራን ያስረዳሉ።

ይሁን እንጂ የፋሺስት ጣሊያን ጦር በአካባቢዉ ጀግኖች ኢትዮጵያዉያን የተባባረ ክንድ ዳግም ድል ተመቷል።

ሳምቤ የጣሊያን የመጨረሻው አውደ ውጊያ መሆኑን የታሪክ ምሁራን ያስረዳሉ።

የኢሉባቦር ዞን ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ኀላፊ አቶ ወንድሙ ደበላ 84ኛው የሳምቤ የአርበኞች ድል መታሰቢያ ነገ በኢሉአባቦር ዞን ጎሬ ከተማ አቅራቢ በሳምቤ እንደሚከበር ተናግረዋል።

የኢሉአባቦር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳልካቸው ተፈሪ በበኩላቸዉ አዲሱ ትዉልድ የቀደምት አባት አርበኞቹን የህብረ ብሄራዊ አንድነት መንፈስ በልማትና በሠላም ስራዎች ዳግም እዉን ሊያደርግ ይገባል ብለዋል።

የመቱ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ተሻለ ኤጀርሶ ሳምቤ ጀግኖች ፋሺስት ጣሊያንን ድል ያደረጉበት ስፍራ የቱሪዝም መስህብና የኢኮኖሚ ምንጭ እንዲሆን ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል።

የአርበኞች መታሰቢያ ቀን ነገ ሚያዝያ 27 ቀን 2017 ዓ.ም በሃገር አቀፍ ደረጃም የሚከበር ሲሆን በአሉን ምክንያት በማድረግ ከንጋቱ 12 ሰዓት ላይ 21 ጊዜ መድፍ እንደሚከበር የመከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።

በወንድማገኝ አሰፋ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review