Pfizer የክትባት ጥምረት አካል በሆነው በGavi በኩል ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ሀገሮች ውስጥ ለህፃናት ክትባት አንድ ቢሊዮንኛውን የሳንባ ምች ኮንጁጌትድ ዶዝ አቅርቧል

You are currently viewing Pfizer የክትባት ጥምረት አካል በሆነው በGavi በኩል ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ሀገሮች ውስጥ ለህፃናት ክትባት አንድ ቢሊዮንኛውን የሳንባ ምች ኮንጁጌትድ ዶዝ አቅርቧል

Pfizer የክትባት ጥምረት አካል በሆነው በGavi በኩል ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ሀገሮች ውስጥ ለህፃናት ክትባት አንድ ቢሊዮንኛውን የሳንባ ምች ኮንጁጌትድ ዶዝ አቅርቧል

  • 1 ቢሊዮንኛው የሳንባ ምች ክትባት መጠን ኢትዮጵያ ውስጥ ተሰጥቷል
  • ከ2010 ጀምሮ፣ Pfizer የሳንባ ምች ክትባቶች ወደ 300 ሚሊዮን እና ከዚያ በላይ ሕፃናትን ለመከተብ የGavi መስፈርት ለሚያሟሉ 57 ሀገሮች ደርሰዋል
  • ትብብሩ በዓለም ዙሪያ የጤና አገልግሎትን በእኩልነት የማግኘት ክፍተትን ለመዝጋት እና መድሃኒቶቻችንን እና ክትባቶቻችንን ለማህበረሰቦች ትርፍን መሰረት ባላደረገ መንገድ ለማቅረብ Pfizer ያለው ቁርጠኝነት አካል ነው።

ኒውዮርክ ፣ ጥቅምት 2024Pfizer ከGavi ባለው ጥምረት 1 ቢሊዮንኛውን የሳንባ ምች ኮንጁጌትድ ክትባት (PCV) መስጠቱን ዛሬ አስታውቋል። ቢሊዮንኛውን ክትባት ኢትዮጵያ ውስጥ ሕፃናትን ከሳንባ ምች በሽታ ለመከላከል በሚያስችለው የብሔራዊ ክትባት መርሃ ግብር ላይ ጥቅም ላይ እንዲውል ተሰጥቷል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ፣ ኒሞንያ ከአምስት ዓመት በታች ለሆኑ ሕፃናት ከፍተኛው የሞት መንስኤ የሆነ ተላላፊ በሽታ ነው። የክትባት ትብብር የሆነው Gavi፣ ዓለም አቀፍ የጤና ድርጅቶችን፣ የክትባት ኢንዱስትሪውን እና ሌሎች ዘርፎችን የሚያሰባስብ የህዝብ እና የግል አጋርነት ሲሆን እንደ ኒሞንያ ላሉ አንዳንድ በዓለማችን በጣም ገዳይ የሆኑ በሽታዎች የክትባት ፍትሃዊነትን እና ዘላቂ ተደራሽነትን የሚያሳድግ ነው።

በ2009፣ Gavi ዘላቂ የገበያ ሁኔታን ለመፍጠር በማሰብ፣ የህዝብ እና የግል የጤና ፋይናንስ ዘዴ የሆነውን የሳንባ ምች የላቀ የገበያ አቅርቦት ቁርጠኝነት (በእንግሊዝኛ ምህፃረ ቃሉ AMC) የመሰረተ ሲሆን፣ ይህም ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ላላቸው የGavi መስፈርትን በሚያሟሉ አገሮች ውስጥ የሚገኙ ህጻናት ከፍተኛ ድጎማ በተደረገበት አቅርቦት በተመጣጣኝ ዋጋ እና በአስተማማኝ ሁኔታ ክትባቶችን ለማቅረብ የማልማት እና የማምረት ኢንቨስትመንት ፋይናንስ ለማግኘት የሚያስችል ነው። Pfizer በAMC ውስጥ ከተሳተፉት የመጀመሪያ አምራቾች አንዱ ነበር። ክትባቶቹ እስካሁን ድረስ የGavi መስፈርቶችን ወደሚያሟሉ 57 አገራት የደረሱ ሲሆን፣ ከ300 ሚሊዮን በላይ ህፃናትን ከኒሞንያ በሽታ ለመጠበቅ እንደረዱ ይገመታል።

Gavi ከ2000 ጀምሮ ከአንድ ቢሊዮን በላይ ሕፃናትን እንዲከተቡ የቻለበት የስኬት ምክንያት በልዩ ሁኔታ ብዙ ባለድርሻ አካላትን የሚያካትት ሞዴል በመከተሉ ነው። የክትባት አምራቾች በዚህ አጋርነት ውስጥ ወሳኝ ሚና የሚጫወቱ ሲሆን ይህም ለክትባቶች አቅርቦት ጤናማና ተመጣጣኝ ገበያዎችን ለመፍጠር እና አዳዲስ የፈጠራ መፍትሄዎችን ለማቅረብ ይረዳናል። ከPfizer ጋር በመሆን ከዚህ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ በመድረሳችን ኩራት ይሰማናል እንዲሁም ወደፊ የሚኖረንን ውጤታማ ትብብር በጉጉት እንጠብቃለን ።” – ዶክተር ሳኒያ ኒሽታር፣ የክትባት አጋር የሆነው የGavi ዋና ሥራ አስፈፃሚ።

በኢትዮጵያ በየዓመቱ ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ ከ40,000 በላይ ሕፃናት በኒሞንያ ይሞታሉ። ይህ በየአመቱ በዚህ የዕድሜ ክልል ውስጥ ከሚሞቱት ውስጥ 20% የሚሆነው የሞት መንስኤ ነው። ከ2020 ጀምሮ፣ Pfizer የሀገሪቱን የክትባት ጥረቶች ለመደገፍ ከ40 ሚሊዮን በላይ የኒሞንያ ክትባቶችን አቅርቧል።

“የሕፃናት የሳንባ ምች ክትባቶች በሀገራችን በጣም አንገብጋቢ ከሆኑት የህዝብ ጤና ችግሮች በአንዱ ላይ ለምናደርገው ትግል ወሳኝ ናቸው ። በGavi ድጋፍ፣ በጣም ተጋላጭ የሆኑ ዜጎቻችንን ለመጠበቅ እነዚህን ክትባቶች ማድረስ ችለናል። የአንድ ቢሊዮንኛው ክትባት በኢትዮጵያ እና በዓለም ዙሪያ ያሉ ሕፃናት ጤናማ የህይወት ጅማሮ እንዲኖራቸው ለመርዳት የPfizer፣ የGavi እና የሌሎች አጋሮች ቁርጠኝነት እና ትብብር አስደሳች ምዕራፍ ነው” ብለዋል፣ በኢትዮጵያ የፌዴራል የጤና ሚኒስቴር፣ የበሽታ መከላከያ ኃላፊ የሆኑት አቶ መልካሙ አያሌው

ዛሬ፣ ከሚመረቱ የ Pfizer ሳንባ ምች ክትባቶች ውስጥ ከ50 በመቶ በላይ የሚሆኑት ከGavi ጋር በመተባበር ዝቅተኛ እና ዝቅ ያለ መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሀገሮች ውስጥ ተደራሽነትን ለመደገፍ ይቀርባሉ።

በዓለም ዙሪያ ያሉ ልጆች ረዘም ያለ እና ጤናማ ሕይወት የመኖር እድል እንዲኖራቸው ለማድረግ ከGavi ጋር ባደረግነው ቀጣይነት ያለው ትብብር እንዲህ ያለ አስገራሚ ምዕራፍ ላይ በመድረሳችን በጣም ደስተኞች ነን ፣ ግን ሥራችን እዚህ ላይ አያበቃም” ብለዋል የPfizer የአዳዲስ ገበያዎች ፕሬዝዳንት የሆኑት ኒክ ላጉኖቪች። “እንደነዚህ ባሉ ትብብሮች እና በዓለም አቀፍ ደረጃ መብቶች ለሆኑ መድኃኒቶች እና ክትባቶች ሁሉ ተደራሽነትን ለማስፋፋት እየሰራ ባለው ‘ለጤናማ ዓለም ትብብር’ ተነሳሽነት፣ ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው 45 ሀገሮች ውስጥ ከዓለም አቀፍ የጤና ድርጅቶች፣ ከመንግስታት እና ከሌሎች ጋር በመተባበር ቀጣይነት ያለው፣ ትርፍን መሰረት ያላደረገ የመድኃኒት እና ክትባቶች ተደራሽነት እንዲኖር እና በጣም ተጋላጭ ለሆኑ አካላት የጤና እኩልነት ክፍተትን ለማጥበብ እንሰራለን።”

የሳንባ ምች AMC ለመጀመሪያ ጊዜ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ፣ ሕፃናትን ከሳንባ በሽታ ለመከላከል በሚደረገው ትግል ውስጥ ጉልህ ለውጥ ተገኝቷል። ዓለም አቀፍ ፒሲቪ ሽፋን በ2010 ከነበረው 10 በመቶ በ2023 ወደ 65 በመቶ አድጓል። ሆኖም፣ ይህ በ2030 እንዲደረስበት ዒላማ ከተደረገው 90 በመቶ የክትባት አጀንዳ አንጻር ዝቅተኛ ሲሆን፣ ይህም ተጨማሪ ሥራ መከናወን እንዳለበት ያመለክታል። እንደ የሳንባ ምች በሽታ ያሉ የክትባት መከላከያ ያላቸውን በሽታዎች ለመከላከል ብዙ ሕፃናት መከተባቸውን ማረጋገጥ ለግለሰቦች የከባድ በሽታ እና ሞት መከላከያ ከማቅረብ የተሻገረ ጉዳይ ነው። የጤና ፍትሃዊነትን በማበረታታት፣ የኢኮኖሚ ምርታማነትንበመጨመር እና በጤና አጠባበቅ ስርዓቶች ላይ የወጪ ጫናን በመቀነስ የማህበረሰቦችን እና የአገሮችን ሁኔታ ከፍ ለማድረግ ሊረዳ ይችላል።

በክትባት ትብብሩ የPfizer ከGavi ጋር መተባበር፣ በዓለም ዙሪያ የጤና ፍትሃዊነት ክፍተቶችን ለመቅረፍ እና የመድኃኒት እና የክትባት ተደራሽነት ለማፋጠን ኩባንያው ያለው ሰፊ ቁርጠኝነት አካል ነው። የPfizer ለጤናማ ዓለም ትብብር ተነሳሽነት በዓለም ዙሪያ ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው በ45 ሀገሮች ለሚኖሩ 1.2 ቢሊዮን ሰዎች ተደራሽነትን ለማሳደግ በአይነቱ የመጀመሪያ ጥረት ነው። በትብብሩ አማካኝነት፣ Pfizer እንቅፋት የሆኑ የስርዓት መሰናክሎችን ለማስወገድ ከመንግስታት አና ሌሎች አካላት ጋር በመተባበር መስፈርት ለሚያሟሉ ሀገሮች በዓለም አቀፍ ደረጃ መብት ለያዝንባቸው መድኃኒቶች እና ክትባቶች ሙሉ ፖርትፎሊዮውን እነዚህ ምርቶች ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች እንዳይደርሱ ቁርጠኛ ነው።

ስለ Pfizer Inc.፦ የታማሚዎችን ህይወት የሚቀይሩ አዳዲስ ውጦች

Pfizer ውስጥ፣ የሰዎችን ህይወት የሚያራዝሙ እና ጤንነታቸውን በከፍተኛ ደረጃ ለማሻሻል የሚረዱ ቴራፒዎችን ለመፍጠር ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ሀብቶቻችንን ተግባር ላይ እናውላለን። አዳዲስ መድሃኒቶችን እና ክትባቶችን ጨምሮ በጤና አጠባበቅ ምርቶች ግኝት፣ ልማት እና ምርት ሂደት የጥራት፣ የደህንነት እና የእሴት ደረጃን የምንወስን ለመሆን እንጥራለን። የPfizer ሰራተኞች በዘመናችን በጣም የተፈሩ በሽታዎችን ለመቋቋም፣ የጤንነት፣ የመከላከል፣ የህክምናዎች እና የፈዋሽነት ደረጃን ከፍ ለማድረግ፣ ባደጉ እና በማደግ ላይ ባሉ ገበያዎች ውስጥ በየቀኑ ይሰራሉ። በዓለም ላይ ካሉ ቀዳሚ የባዮፋርማሲካል የፈጠራ ኩባንያዎች አንዱ እንደመሆናችን፣ ሀላፊነታችንን ለመወጣት በዓለም ዙሪያ አስተማማኝና ተመጣጣኝ የጤና እንክብካቤ ተደራሽነትን ለመደገፍ እና ለማስፋት ከጤና አገልግሎት አቅራቢዎች፣ ከመንግስት እና ከአከባቢ ማህበረሰቦች ጋር በመተባበር እንሰራለን። ለ175 ዓመታት፣ በእኛ ላይ ለሚተማመኑ ሁሉ ለውጥ ለማምጣት ሠርተናል። በሚከተለው በድረ ገፃችን ላይ ለባለሀብቶች አስፈላጊ ሊሆኑ የሚችሉ መረጃዎችን በመደበኛነት እንለጥፋለን www.Pfizer.com ። በተጨማሪም፣ ስለ እኛ ለማወቅ፣ እባክዎ በሚከተሉት መንገዶች ይጎብኙን www.Pfizer.com እንዲሁም X ላይ በ @Pfizer እና @Pfizer NewsLinkedInYouTube ያግኙን እንዲሁም Facebook ላይ Facebook.com/Pfizer ይወዳጁን።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review