World Without Hunger የተሰኘ አለም አቀፍ ጉባኤ ከጥቅምት 26-28 በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው

You are currently viewing World Without Hunger የተሰኘ አለም አቀፍ ጉባኤ ከጥቅምት 26-28 በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው

AMN- ጥቅምት 8/2017 ዓ.ም

ከረሃብ ነፃየሆነች አለም መፍጠር ይቻላል በሚል መርህ የሚከናወነው World Without Hunger የተሰኘው አለም አቀፍ ጉባኤ ከጥቅምት 26-28 በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው

ጉባኤውን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት (UNIDO)፣ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን (AUC) እና በኢትዮጵያ መንግስት እና በአለም ምግብ ድርጅት (FAO) ትብብር የሚዘጋጅ ነው።

ረሃብ እና የተመጣጠነ ምግብ እጥረት በሰው ልጅ ላይ ከተጋረጡ ዋና ዋና ተግዳሮቶች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው።

በአለም አቀፍ ደረጃ የተቀመጡትን ዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት ደግሞ ረሃብ እና የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ለማስወገድ በሁሉም ባለድርሻ አካላት መካከል የተቀናጀ ጥረት ማድረግ ይጠይቃል።

የረሃብ የሌለበት አለም የመፍጠር አላማ ያደረገው ይሄው ኮንፈረንስ ለችግሮቹ የመፍትሄ ሃሳቦችን በሚያመላክት ፣ ቴክኒካዊና በኢንቨስትመንት ጉዳዮች እንዲሁም ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ በማተኮር ውይይቱን ለሶስት ቀናት በአዲስ አበባ ያካሂዳል ተብሎ ይጠበቃል።

በጉባኤው ከ1 ሺህ 500 በላይ ተሳታፊዎች ታዳሚ እንደሚሆኑም ይጠበቃል ፡፡

በጉባኤው ላይ ሚኒስትሮች ፣ የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች ፣ የተመድ ኤጀንሲዎች ሀላፊዎች ፣ የግል ባለሀብቶች ፣ የፋይናንስ ተቋማት ፣ ለጋሽ ድርጅቶች፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትና የመገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ይገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከዩኒዶ ማህበራዊ የትስስር ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review