ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በቀጣዩ አንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ቀሪ ተግባራትን ያጠናቅቃል -ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ

You are currently viewing ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በቀጣዩ አንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ቀሪ ተግባራትን ያጠናቅቃል -ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ

AMN – የካቲት 13/2017 ዓ.ም

ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በቀጣዩ አንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ቀሪ ተግባራትን በማጠናቀቅ አጀንዳዎችን የመቅረፅና ይፋ የማድረግ ስራ እንደሚያካሂድ ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ አስታወቁ።

ኮሚሽኑ ያለፉት ሶስት አመታት የስራ ክንውኑን እና የቀጣይ ዓመት ተግባራቱን አስመልክቶ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ፥በዚሁ ወቅት እንደገለፁት ኮሚሽኑ በቀጣይ አንድ ዓመት ውስጥ ቀሪ ተግባራትን በማጠናቀቅ ምክክር ለማካሔድ ይሰራል።

በተጨማሪም የዳያስፖራ አካላት ተሳታፊዎች ልየታ የሚካሂድ ሲሆን፤ የምክክር ጉባኤ ተሳታፊዎችን የማስወከል ስራም እንደሚከናወን ገልጸዋል።

በዚህም በቀጣይ አንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ አጀንዳዎችን የመቅረፅና ይፋ የማድረግ አማካሪዎችን እና አመቻቾችን የመለየት ስራም እንደሚካሔድ ነው የጠቆሙት።

ከሚካሔደው ምክክር የሚገኝ ምክረ ሀሳብን የማጠናቀርና ምክረ ሀሳቡን የማቅረብ ስራ እንደሚከናወንም መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ሀገር አቀፍ ንቅናቄ በማካሔድ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች እንደሚከናወኑም አስታውቀዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review