ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልዕክት ሀገራዊ የብልፅግና ግባችንን እና ዓመታዊ እቅዶቻችንን ለማሳካት ተቋማት ቀን ከሌት ሊተጉ ይገባል ብለዋል።
የ2017 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት ዋና ዋና የማክሮ ኢኮኖሚ እና የዘርፎችን ዕቅድ አፈጻጸም ዛሬ ከፌደራል ተቋማት የስራ ኃላፊዎች ጋር መገምገም ጀምረናል።
በቆይታችንም በ100 ቀናት የትኩረት ማዕከል የሆኑ ዋና ዋና ተግባራት፣ የተገኙ ውጤቶችን፣ የታዩ ክፍተቶችን እና የትኩረት አቅጣጫዎች ከተቋማቱ የስራ ኃላፊዎች ጋር በጋራ እናያለን።
ባለፉት ዘጠኝ ወራት በተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ እና ሪፎርም ትግበራ በተለያዩ መስኮች በርካታ ስኬቶች ተመዝግበዋል። የዘርፎች አፈጻጸምም የላቀ ነው። እነዚህ ድሎቻችን እንደ መንግስት የመፈፀም አቅማችንን ማሳያዎች ናቸው።
በመሆኑም በቀሪ ወራት መፈፀም ያለባቸውን ተግባራት በመለየት በዓመቱ ለማሳካት የተያዙ ትልሞችን በተሟላ መልኩ ለመፈፀም ሁሉም አካላት በትኩረት መስራት ይገባቸዋል ብለዋል።