ሁለት የመንግስታት ጥምረቶች ከቻይና ጋር እየመከሩ ነው

You are currently viewing ሁለት የመንግስታት ጥምረቶች ከቻይና ጋር እየመከሩ ነው

AMN- ግንቦት 19/2017 ዓ.ም

የደቡብ ምስራቅ እስያ መንግስታት ማህበር እና የባህረ ሰላጤው የትብብር ምክር ቤት አባል ሀገራት ፤ ከቻይና ጋር ያላቸውን የንግድ ትብብር ለማጠናከር ያለመ ውይይት እያካሄዱ ነው።

በማሌዢያ ዋና ከተማ ኩዋላ ላምፑር እየተካሄደ ባለው ጉባኤ ላይ ሀገራቱ ንግዳቸውን ከአሜሪካ ጥገኝነት ለማላቀቅ የሚያስችል መፍትሔ እንደሚፈልጉ ተነግሯል።

ሁለቱ የመንግስታት ጥምረቶች በአሜሪካ የታሪፍ ጭማሪ ከፍተኛ መናወጥ የገጠመውን የዓለም የንግድ ሥርዓት ለመቋቋም ከቻይና ጋር መላ ለመምታት እየመከሩ ነው።

የማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር ኢብራሂም፣ በጉባኤው መክፈቻ ላይ የሁለቱ ጥምረቶች ጠንካራ ግንኙነት ቀጣናዊ ትብብርን ለማሳደግ እና ዘላቂ ብልፅግናን ለማረጋገጥ ቁልፍ ሚና እንደሚጫወት መናገራቸውን አልጀዚራ ዘግቧል።

የደቡብ ምስራቅ እስያ መንግስታት ብሩኒ፣ ካምቦዲያ፣ ኢንዶኔዥያ፣ ላኦስ፣ ማሌዥያ፣ ማይንማር፣ ፊሊፒንስ፣ ሲንጋፖር፣ ታይላንድ እና ቬትናም ያቀፈ ማህበር ነው።

የባህረ ሰላጤው የትብብር ምክር ቤትም ባህሬንን፣ ኩዌትን፣ ኦማንን፣ ኳታርን፣ ሳዑዲ አረቢያን እና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስን አቅፏል።

በኢዮብ መንግስቱ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review