ሁሉንም የሚያግባባ ሀገረ መንግስት ለመገንባት የሽግግር ፍትህ ፖሊስን ተግባራዊ ማድረግ የማይተካ ሚና አለው :- የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት

AMN ህዳር 23/2017 ዓ.ም

ሁሉንም የሚያግባባ ሀገረ መንግስት ለመገንባት የሽግግር ፍትህን ፖሊስን ተግባራዊ ማድረግ የማይተካ ሚና እንደሚኖረው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ረዳት ተጠሪ ሚንስትር ዴኤታ ወ/ሮ መሰረት ኃይሌ ገለፀዋል።

በሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ላይ ለሴት የምክር አቤት አባላት የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በአዲስ አበባ ተካሄዷል።

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የመንግስት ረዳት ተጠሪ ሚንስትር ዴኤታ ወ/ሮ መሰረት ሀይሌ እንደተናገሩት፤ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ የሚመራበትን እና የሚተገበርበትን ሥርዓት በመዘርጋት ዘላቂ ሰላምን ማስፈን እንዲሁም የሕግ የበላይነትን ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።

ፖሊሲውን ተግባራዊ በማድረግ ከእርስ በእርስ ግጭት ወደ የተረጋጋ ሠላም እና የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ መሸጋገር እንደሚገባም ገልፀዋል።

ባለፉት 6 ዓመታት በተደረጉ ሀገራዊ ፎርሞች የተረጋጋ ሀገር መንግስት ለመገንባት ማነቆ ሆነው የቆዩ ፖሊሲዎችን፣ ሕጎችን፣ አደረጃጀቶችን በመቀየር እና በማሻሻል ሀገሪቱን በኢኮኖሚዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ዘርፎች ከፍ ወዳለ ደረጃ ማድረስ እንደሚገባም አብራርተዋል።

ፖሊሲው የሀገርዊ ሪፎረሙ አካል ነው ያሉት ወ/ሮ መሰረት፤ ፍትህ በማስፈንና ዕርቅን በማውረድ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ በትኩረት መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የምክር ቤቱ ሴት ተመራጮች (የሴቶች ኮክስ) የሕግ የበላይነትን በማረጋገጥ ሴቶችና ህፃናትን ብሎም መላውን ህዝብ ከጥፋት ለመታደግ እና የፍትሕ ሥርዓቱን ፍትሐዊ እንዲሆን ለማድረግ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡም የመንግስት ረዳት ተጠሪዋ አሳስበዋል።

በተጨማሪም ለወከላቸው ማህበረሰብ ግንዛቤ በመፍጠር እንዲሁም የሕግ የበላይነትን በማረጋገጥ ተጠያቂነትን ለማስፈን እና የተጎዱ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም በሚደረገው ሀገራዊ ውሳኔና እንቅስቃሴ የድርሻቸውን ሚና እንዲወጡ አስገንዝበዋል።

በመድረኩ የመንግስት ረዳት ተጠሪን ጨምሮ የፍትህ ሚኒስቴር ሚንስትር ወ/ሮ ሀና አርአያስላሴ፣ የሴቶች ኮክስ አመርሮችና አባላት እንዲሁም ኮናርድ አድናዎር ሲቲፍቱንግ ሴቶች ላይ የሚሰራ አለማቀፍ ድርጅት አመራሮች መገኘታቸውን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለከትታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review