AMN – ጥር 8/2017 ዓ.ም
በካናዳ የሥራ እና ትምህርት ዕድል ለማመቻቸት ህጋዊ ውክልና በውጭ ጉዳይ ሚኒስት ጌዲዮን ጢሞትዮስ (ዶ/ር) የተሰጣቸው በማስመሰል ህገ ወጥ ደብዳቤ አዘጋጅተው እያሰራጩ ያሉ አካላት መኖራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል፡፡
የሚኒስትሩ ስም ተጠቅሶ በተለያዩ የማህበራዊ ሚድያ አውታሮች እየተዘዋወረ የሚገኘው ደብዳቤ ሀሰተኛ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
እንዲህ አይነቱን የወንጀል ተግባር እየፈፀሙ የሚገኙ አካላትን በህግ ተጠያቂ ለማድረግ ከሚመለከታቸው ጋር እየተሰራ መሆኑን ሚኒስቴሩ አመልክቷል።
ህብረተሰቡም ይህንን ተገንዝቦ ራሱን ከአጭበርባሪዎች እንዲጠብቅ ማሳሰቡን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።