AMN-መጋቢት 1/2017 ዓ.ም
ህብረተሰቡ መንግስት የቀየሳቸውን የልማት ስትራተጂዎች ለማሳካት የሚያደርገውን ተሳትፎ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) ገለጹ።
ሚኒስትሩ በአርሲ ዞን መርቲ ወረዳ በአቦምሣ ምርጫ ክልል ከሚኖሩ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ተወያይተዋል።
ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የሀገሩን እና የራሱን ህይወት ለማሻሻል መንግስት የቀየሳቸውን የልማት ስትራቴጂዎች ተግባራዊ ለማድረግ እየተረባረበ መሆኑን ያነሱት ሚኒስትሩ፣ ይህም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
በተለይም ወጣቱ ክፍል ራሱን ከአላስፈላጊ ነገሮች ጠብቆ በተለያዩ ልማቶች በመሳተፍ የኢኮኖሚ ብልፅግናን ለማረጋገጥ የሚያደርገው ጥረት ከፍተኛ መሆኑን ማድነቃቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።