ህብረተሰቡ የትንሳኤ በዓልን ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲያከበር አስፈላጊው ዝግጅት ተጠናቋል – የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ

You are currently viewing ህብረተሰቡ የትንሳኤ በዓልን ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲያከበር አስፈላጊው ዝግጅት ተጠናቋል – የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ

AMN – ሚያዝያ 07/2017

ህብረተሰቡ የትንሳኤ በዓልን ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲያከበር አስፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ፡፡

ቢሮው የትንሳኤ በዓል በሰላም እና ከህገወጥ እንቅስቃሴዎች በጸዳ መልኩ እንዲከበር የሚያስችል የውይይት መድረክ ከባለድርሻ አካላት ጋር አካሂዷል።

በዓልን ተከትሎ የዋጋ ጭማሪ እንዳይደረግ እና የንግድ ስረዓቱ ህግን የተከተለ እንዲሆን በርካታ ስራዎች መከናወናቸውን እና ተጨባጭ ውጤትም መገኘቱን ጠቁመዋል።

ከአቅርቦት አንጻር ችግር ሳይኖር ችግር እንዳለ በማስመሠል ሰው ሰራሽ የምርት እጥረት የፈጠሩ አካላት ላይ እርምጃ በመውሰድ ማረም መቻሉንም ኃላፊዋ ገልጸዋል።

በገበያ ማዕከላት እና የንግድ እንቅስቃሴ በሚካሄድባቸው አካባቢዎች የሚደረጉ የቁጥጥር ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉም ብለዋል።

ህገወጥ እርድ እና ተረፈ ምርት አወጋገድ ላይም የቁጥጥር ስራ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ እንደሚገኝም ተገልጿል፡፡

በሀብታሙ ሙለታ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review