ህዝበ ሙስሊሙ የረመዳን ወርን የእምነቱ አስተምህሮ በሚያዘዉ መሰረት በመረዳዳትና በመተሳሰብ እንዲያሳልፍ ጥሪ ቀረበ

You are currently viewing ህዝበ ሙስሊሙ የረመዳን ወርን የእምነቱ አስተምህሮ በሚያዘዉ መሰረት በመረዳዳትና በመተሳሰብ እንዲያሳልፍ ጥሪ ቀረበ

AMN – የካቲት 21/2017 ዓ.ም

ህዝበ ሙስሊሙ የረመዳን ወርን የእምነቱ አስተምህሮ በሚያዘዉ መሰረት በመረዳዳትና በመተሳሰብ እንዲያሳልፍ የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ጥሪ አቀረበ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የ1446ኛውን የረመዳን ወርን አስመልክቶ በዛሬው ዕለት መግለጫ ሰጥቷል፡፡

የምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት ሼህ ሱልጣን አማን ኤባ፣ ለ1446ኛው የረመዳን ወር የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን፣ ህዝበ ሙስሊሙ በዚህ ታላቅ ወር ተቻችሎ እና አንድነቱን ጠብቆ በፀሎት ላይ ትኩረት በመስጠት ወደ አላህ በመመለስ እንዲያሳልፍ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ፕሬዝዳንት ሼህ ሱልጣን አማን ኤባ፣ ህዝበ ሙስሊሙ በረመዳን ወር የታመሙትን በመጠየቅ፣ ወላጅ የሌላቸውን እና የተቸገሩትን በመርዳት እንዲያሳልፍ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የረመዳን ፆም ዛሬ ጨረቃ ከታየች ቅዳሜ፣ ካልታየች ደግሞ እሑድ እንደሚጀምርም ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል።

በመሀመድኑር አሊ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review