ህዝቡ ሚዛናዊ አስተሳሰብ ያዳበረና ለልማቱ ያለውን ቁርጠኛ ፍላጎት በተጨባጭ ማሳየቱን ተገንዝበናል- አቶ ማሾ ኦላና

You are currently viewing ህዝቡ ሚዛናዊ አስተሳሰብ ያዳበረና ለልማቱ ያለውን ቁርጠኛ ፍላጎት በተጨባጭ ማሳየቱን ተገንዝበናል- አቶ ማሾ ኦላና

AMN – መጋቢት 30/2017 ዓ.ም

ህዝቡ ሚዛናዊ አስተሳሰብ ያዳበረና ለልማቱ ያለውን ቁርጠኛ ፍላጎት በተጨባጭ ያሳየ መሆኑን መገንዘብ ችለናል ሲሉ በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ማሾ ኦላና ተናገሩ፡፡

በአዲስ አበባ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች የመራጭ ተመራጭ መድረኮች ተከናውነዋል፡፡

በተመረጡበት በጉለሌ ክፍለ ከተማ ተገኝተው የውይይት መድረኩን ያጠቃለሉት በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ማሾ ኦላና፣ በዛሬው ዕለት በአስሩም ክፍለ ከተሞች በተካሄዱ የመራጭ ተመራጭ መድረኮች ህዝቡ ሚዛናዊ አስተሳሰብ ያዳበረና ለልማቱ ያለውን ቁርጠኛ ፍላጎት በተጨባጭ ያሳየ መሆኑን መገንዘብ ችለናል ብለዋል።

በተለይ የተጀመረው የልማት ስራ እጅግ ተስፋ ሰጪ እና አጓጊ በመሆኑ በዚሁ እንዲቀጥል ምክርቤቱ የበኩሉን ድጋፍ እንዲያደርግ ህዝቡ ጥሪ ማቅረቡን ጠቁመዋል፡፡

የመልካም አስተዳደር እና አገልግሎት አሰጣጡን ዘመናዊ እና ከብልሹ አሰራር የፀዳ ለማድረግ የሚደረገው ጥረትም የተሻለ መሆኑና ተጠናክሮ እንዲቀጥል ህዝቡ አጋር እንዲሆን አሳስበዋል።

በሌላ በኩል የኑሮ ውድነቱን ከመቅረፍ አንፃር ተጨማሪ ስራ እንደሚጠይቅ በተመሳሳይ የመልካም አስተዳደርና አገልግሎት አሰጣጡ የተሻሻለ ነገር ቢኖርም አሁንም በትኩረት የሚሰራ እንደሚሆን ግንዛቤ መያዙን አመላክተዋል።

በመርሐ-ግበሩም የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ምሁራን፣ ሴቶች፣ ወጣቶች፣ የምክርቤት አባላትን ጨምሮ ከአሥሩም ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ ከ5 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች መሳተፋቸውን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review