ህዝቡ የሚያነሳቸው ጥያቄዎች በየደረጃዉ ምላሽ እንዲያገኙ ትኩረት ተሰጠቶ ይሰራል – አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር

You are currently viewing ህዝቡ የሚያነሳቸው ጥያቄዎች በየደረጃዉ ምላሽ እንዲያገኙ ትኩረት ተሰጠቶ ይሰራል – አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር

AMN – መጋቢት 30/2017

ህዝቡ የሚያነሳቸው ጥያቄዎች በየደረጃዉ ምላሽ እንዲያገኙ ትኩረት ተሰጠቶ እንደሚሰራ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር ተናገሩ::

ህዝብን እና መንግስትን በማቀራረብ በአስፈፃሚው በኩል ለሕዝብ ተገቢውን ምላሽ እንዲሰጥ የሚያደርጉት የምክር ቤት አባላት በተመረጡበት አካባቢዎች ከህዝብ ጋር በመገናኘት የህዝቡን ጥያቄ እያደመጡ ይገኛል::

በየካ ክፍለ ከተማ የአዲስ አበባ ምክር ቤት ተመራጮችም ከክፍለ ከተማው ነዋሪ ጋር ምክክር እያደረጉ ነው::

በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልከደርን ጨምሮ ክፍለ ከተማውን ወክለዉ ለአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የተመረጡ የምክር ቤት አባላት ተገኝተዋል ::

ወ/ሮ ቡዜና አልከድር በዚህ ወቅት እንዳሉት፣ ህዝቡ ከዚህ በፊት ሲያነሳቸዉ የነበሩ ጥያቄዎች ከአስፈፃሚ አካላት ጋር በመሆን ምላሽ እንዲያገኙ መደረጉን ተናግረዋል::

በቀጣይም ህዝቡ የሚያነሳቸው ጥያቄዎች በየደረጃዉ ምላሽ እንዲያገኙ ትኩረት ተሰጠቶ ይሰራልም ብለዋል::

በመድረኩም ባለፉት ጊዚያት የተከናወኑ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችና የተከናወኑ የልማት ስራዎች ሪፖርት ቀርቧል::

በቴዎድሮስ ይሳ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review