ለ2017/18 የምርት ዘመን ከተገዛው 2.4 ሚለዮን ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ ከ614 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ የሚሆነው ወደ ሀገር ውስጥ ተጓጉዟል- ሚኒስቴሩ

You are currently viewing ለ2017/18 የምርት ዘመን ከተገዛው 2.4 ሚለዮን ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ ከ614 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ የሚሆነው ወደ ሀገር ውስጥ ተጓጉዟል- ሚኒስቴሩ

AMN – የካቲት 17/2017 ዓ.ም

ለ2017/18 የምርት ዘመን ግብዓት የሚሆን ከተገዛው ሃያ-አራት ሚሊዮን ኩንታል ወይም 2.4 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ እሰከ የካቲት 16 ቀን 2017 ዓ.ም 614 ሺህ 865.2 ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ መጓጓዙን ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በ12 መርከቦች ከተጫነው ውስጥ በ7 መርከቦች 401 ሺህ 400 ሜትሪክ ቶን ዳፕ እንዲሁም በ5 መርከቦች የተጫነው ደግሞ 239 ሺህ 795.1 ሜትሪክ ቶን ዩሪያ የተሰኘው የአፈር ማዳበሪያ መሆኑም ተመላክቷል፡፡

ከ377 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ ዳፕ እንዲሁም ከ237 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ ደግሞ ዩሪያ የተሰኘው የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ እንደተጓጓዘ ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወደ ሀገር ውስጥ ከተጓጓዘው 614 ሺህ 865.2 ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ 90 ሺህ 965 ሜትሪክ ቶኑ በባቡር፣ ቀሪው 523 ሺህ 900.2 ሜትሪክ ቶኑ ደግሞ የተጓጓዘው በድንበር ተሻጋሪ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎች አማካኝነት መጓጓዙም ተገልጿል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review