ለ2017/18 የምርት ዘመን የአፈር ማዳበሪያ ከውጭ ማጓጓዝ ተጀመረ

You are currently viewing ለ2017/18 የምርት ዘመን የአፈር ማዳበሪያ ከውጭ ማጓጓዝ ተጀመረ

AMN – ጥቅምት 29/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በ2017/18 የምርት ዘመን ከውጭ ከሚገዛው 23 ሚሊየን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ 472 ሺህ 500 ኩንታል ዩሪያ የጫነች የመጀመሪያዋ ኤም ቪ አባይ ሁለት የተሰኘች የኢትዮጵያ መርከብ ጂቡቲ ወደብ መድረሷ ተገልጿል።

በቀጣይ ቀናትም ተጨማሪ ማዳበሪያ የጫኑ መርከቦች ጂቡቲ ወደብ እንደሚደርሱ እና ወደ ሀገር ውስጥ የማጓጓዝ ሥራውም በፍጥነት እንደሚጀመር ይጠበቃል።

ለ2017/18 የምርት ዘመን ለሚውል 23 ሚሊየን ኩንታል ዩሪያ እና ዳፕ የአፈር ማዳበሪ ግዥ 1.3 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር በመንግሥት መፈቀዱ ይታወሳል።

መንግሥት በአፈር ማዳበሪያ ግዥ ላይ ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገ አዲስ የግዥ መመሪያ በማውጣቱ እና ከግዥ ጋር የተያያዙ ችግሮች በመፈታታቸው ባለፈው የምርት ዘመን 21 ቢሊየን ብር ለማዳን መቻሉን የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

የግብርና ሚኒስቴር በየዓመቱ እያጠና በሚያቀርበው የሀገሪቱ የአፈር ማዳበሪያ ፍላጎት መሰረት የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢግሥኮ) ከተቋቋመበት ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ ዓለም አቀፍ ጨረታ እያወጣ የማዳበሪያ ግዥ በመፈጸም ላይ ይገኛል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review