ለኢሬቻ በዓል የትራንስፖርት እጥረት እንዳይፈጠር ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል-የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር

You are currently viewing ለኢሬቻ በዓል የትራንስፖርት እጥረት እንዳይፈጠር ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል-የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር

AMN – መስከረም 23/2017 ዓ.ም

በመጪው ቅዳሜና እሑድ በሆራ ፊንፊኔ እና በሆራ አርሰዲ ለሚከበረው የኢሬቻ በዓል የትራንስፖርት እጥረት እንዳይፈጠር ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በሆራ ፊንፊኔ ለሚከበረው የኢሬቻ በዓል በተለያዩ አቅጣጫ ከኦሮሚያ ክልል ለሚመጡት ተሳታፊዎች ከኦሮሚያ ትራንስፖርት ቢሮ ጋር በመሆን የትራንስፖርት አቅርቦቱ እንዲጨምር ለማድረግ በቅንጅት እየተሰራ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

የበዓሉ ታዳሚዎች በአዲስአበባ ከተማ ውስጥ ለሚያደርጉት እንቅስቃሴ እና ከፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል አከባበር በኃላ ወደ ቢሾፍቱ ለሚደረገው ጉዞ ፣ እንዲሁም የሆራ አርሰዲ የኢሬቻ በዓል ሲጠናቀቅ ወደ አዲስ አበባ እና ወደ ተለያዩ ቦታዎች ለመንቀሳቀስ የትራንስፖርት እጥረት እንዳያጋጥም የአዲስ አበባ የከተማ አውቶብስ ፣የአገር አቋራጭ አውቶብሶች እና መለስተኛ ተሽከርካዎችን በበቂ ሁኔታ ለማቅረብ ከአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ጋር በመሆን ከወዲሁ የማመቻቸት እንቅስቃሴ እየተደረገ እንደሚገኝ ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review