
AMN-ግንቦት 19/2017 ዓ.ም
ትናንት ከደጋፊዎች ጋር የፕሪምየር ሊግ ድላቸውን ሲያከብሩ የነበሩት ሊቨርፑሎች መጨረሻ ላይ በደረሰ አደጋ ደስታቸው ወደ ሀዘን ተቀይሯል፡፡
አንድ የ53 ዓመት ግለሰብ ሰዎች ወደ ተሰባሰቡበት ቦታ መኪና በመንዳት በርካቶችን ለጉዳት ዳርጓል፡፡ እንደ መርሲሳይድ ግዛት ፖሊስ እስካሁን 47 ሰዎች ጉዳት ገጥሟቸዋል፡፡
የ20ዎቹ ጉዳት ቀለል ያለ በመሆኑ ወደ ቤታቸው አቅንተዋል፡፡ 27ቱ ግን ወደ ሆስፒታል ተወሰወደዋል፡፡ ሆስፒታል ካቀኑት ውስጥ አራቱ ጉዳታቸው የከፋ እንደሆነ የደይሊ ሜል ዘገባ ያሳያል፡፡ እስካሁን ሕይወቱን ያጣ ግለሰብ እንደሌለም ተነግሯል፡፡

ሊቨርፑል የፕሪምየር ሊጉን ድል ተከትሎ የተለያዩ መርሃግብሮችን የያዘ ሲሆን ለጊዜው እቅዶቹን እንደሰረዘ ተነግሯል፡፡ ክለቡ ይበልጥ ተጎጂዎችን መንከባከብ ላይ ትኩረት አድርጓል፡፡ ተጎጂዎች ያሉበትን ሁኔታ በቅርበት እየተከታተለ እንደሚገኝም አሳውቋል፡፡
ሊቨርፑል በተለየ ሁኔታ የፕሪምየር ሊግ የዋንጫ ድሉን ከሰራተኞቹ ጋር ለማክበር እየተሰናዳ ነበር፡፡
በሸዋንግዛው ግርማ