መንግስት በገባው ቃል መሰረት በሁሉም ዘርፍ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች ተቀርፀው ስራ ላይ እየዋሉ ነው፡-ወንድሙ ሴታ (ኢንጅነር)

You are currently viewing መንግስት በገባው ቃል መሰረት በሁሉም ዘርፍ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች ተቀርፀው ስራ ላይ እየዋሉ ነው፡-ወንድሙ ሴታ (ኢንጅነር)

AMN – ታኅሣሥ 29/2017 ዓ.ም

መንግስት በገባው ቃል መሰረት በሁሉም ዘርፍ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች ተቀርፀው ስራ ላይ እየዋሉ ነው ሲሉ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ወንድሙ ሴታ (ኢንጅነር) ገለጹ፡፡

በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ አስተዳደር የሚገኘው 21ኛው ተስፋ ብርሀን የምገባ ማዕከል በረከት ገበሬዋ ቅርንጫፍ የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ከ500 በላይ በጎዳና ላይ ለሚገኙ እና ለአቅመ ደካማ ወገኖች ምሳ የማብላት ፣አልባሳት የማልበስ እና ልዩ የበአል መዝናኛ ዝግጅት መርሀ-ግብር ተካሂዷል።

በመረሃ ግብሩ ላይ የተገኙት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ እንደተናገሩት መንግስት በገባው ቃል መሰረት በሁሉም ዘርፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶች ተቀርፀው ስራ ላይ እየዋሉ እና የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰራ ነው፡፡

በበዓላት ወቅት የሚጎበኛቸው ከሌላቸው ወገኞች ጋር በዓልን ማሳለፍና አለንላችሁ ማለት ያስፈልጋል ያሉት ዋና ስራ አስኪያጁ ኢትዮጰያዊ ባህላችን የሆነውን የመረዳዳትና የአብሮነት ባህልንም አቅመ ደካሞችን በመጎብኘት በጋራ ማእድ በመቋደስ አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል፡፡

ሰው ተኮር ተግባራትን አጠናክረን የህብረተሰባችንን ጥያቄ እንመልሳለን ያሉት ደግሞ የኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ኒዕመተላህ ከበደ ናቸው፡፡

የአንድነት የመተሳሰብ እና አብሮ የመኖር እሴቶቻችንን ከማጠንከር ጎን ለጎን ማእድን አብሮ መቋደስ ደግሞ የበለጠ ያስደስታል ብለዋል፡፡

እነዚህን እሴቶቻችንን የበለጠ በማጠናከር ወንድማማችነትንና ህብረትን ማጎልበት ይኖርብናልም ብለዋል።

የገና በዓልን ስናከብር እንደተለመደው እርስ በርስ በመተሳሰብ በመደጋገፍ እና በመረዳዳት ሊሆንም ይገባል ብለዋል፡፡

ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ድጋፍ ያደረጉ በጎ ፍቃደኞችን ማመስገናቸውን ከክፍለ ከተማው ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review