መንግስት ከማህበረሰቡ ጋር ቀርቦ የሚሰራበት መንገድ የሚደነቅ ነው-የዩኤንዲፒ የአፍሪካ ቀጣና ዳይሬክተር አሁና ኤዚያኮንዋ

You are currently viewing መንግስት ከማህበረሰቡ ጋር ቀርቦ የሚሰራበት መንገድ የሚደነቅ ነው-የዩኤንዲፒ የአፍሪካ ቀጣና ዳይሬክተር አሁና ኤዚያኮንዋ

AMN-የካቲት 9/2017 ዓ.ም

የዩኤንዲፒ ረዳት ዋና ፀሃፊ እና የአፍሪካ ቀጣና ዳይሬክተር አሁና ኤዚያኮንዋ እና የኢትዮጵያ ካንትሪ ዳይሬክተር ሳም ዱዎ ገላን ጉራ መኖርያና የተቀናጀ የልማት መንደርን ጎብኝተዋል።

በጉብኝታቸው ለልማት ተነሺዎች የተፈጠረዉን የመሰረተ ልማት ምቹ ሁኔታ የስፖርት ማዘዉተርያ ስፍራ፣ የህፃናት መጫወቻ ሜዳዎች ከተሟላ መጫወቻ ጋር፣ ከቅድመ መደበኛ እስከ 2ኛ ደረጃ ያሉ ግንባታቸው በ57 ቀናት ዉስጥ ተጠናቆ አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ ት/ቤቶች እንዲሁም ሌሎች የልማት ፕሮጀክቶችን ተመልክተዋል።

የልማት ተነሺዎች አሁን ያሉበት የኑሮ ሁኔታ በመኖርያ ቤታቸው በመገኘት ተዘዋውረው መጎብኘታቸው ተገልጿል።

የአፍሪካ ቀጠና ዳይሬክተርዋ አሁና ኤዚያኮንዋ፣ በተመለከቱት ሰው ተኮር የልማት ፕሮጀክቶች ደስተኛ መሆናቸውን እና መንግስት ከማህበረሰቡ ጋር ቀርቦ የሚሰራበት መንገድ የሚደነቅ መሆኑን ገልፀዋል።

ነዋሪዎችም ከዚህ ቀደም የነበራቸው የአኗኗር ዘይቤና ይኖሩበት የነበረዉ ስፍራ ለሰው ልጅ ክብር የማይመጥን፣ ለጤናም ከፍተኛ ስጋት የነበረው መሆኑን አስታውሰዋል።

አሁን ላይ በተመቻቸላቸው የተሟላ መሰረተ ልማት እና ሰው ተኮር የልማት ስራዎች ደስተኞች መሆናቸውን በጉብኝቱ ወቅት መግለጻቸውን የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያሳያል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review