መንግስት ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር እያደረገ ያለው ውይይት ለነዋሪው እና ለመንግስት ጠቃሚ ነው

AMN- ግንቦት 13/2017 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ መንግስት ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር እያደረገ ያለው ውይይት ለነዋሪው እና ለመንግስት ጠቃሚ ነው ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት እና ኮሙኒኬሽን መምህር ጌታቸው ድንቁ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ዶክተር ጌታቸው ድንቁ በተለይም ለኤ ኤም ኤን ኤፍ ኤም 96.3 እንደገለጹት፣ ብዙሃን መገናኛ ዘዴዎችም በትክክል የተነሱትን እና በቀጣይ እንዲሠሩ የተጠየቁትን ማድረስ ተገቢ ነው ብለዋል።

ብዙሃን መገናኛ ዘዴዎች ሚዛኑን የጠበቀ ዘገባ ከሠሩ ተጠቃሚው ሕዝቡም መንግስትም እንደሚሆኑ አንስተዋል።

ለአድማጭ ተመልካቾች መረጃን ተደራሽ የሚያደርጉ መገናኛ ብዙሃን በሚዛኑ ሊዘግቡ ይገባል ያሉት ዶክተር ጌታቸው፣ መረጃዎችን በልኩ ተደራሽ አለማድረግ ሙያዊ ስነ ምግባርን ያለመወጣት በመሆኑ ተጠያቂነት የሚያስከትል መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

በእውነተኛ መረጃ ላይ የተመሰረተ ዘገባ በተሠራ ቁጥር በመንግስት እና በዜጋው መካከል መቀራረቦች ይፈጠራሉ ብለዋል፡፡

በሲሳይ ንብረቱ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review