መዲናዋን የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ የተሰሩ ሰራዎች የሚደነቁ ናቸው- አቶ አረጋ ከበደ

You are currently viewing መዲናዋን የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ የተሰሩ ሰራዎች የሚደነቁ ናቸው- አቶ አረጋ ከበደ

AMN – ጥር 22/2017 ዓ.ም

የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች እና አባላት በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት አመታት የተሰሩ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነው፡፡

ከተማዋን የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ የተሰሩት የአዲስ አፍሪካ ኤግዚቢሽንና ኮንቬሽን ማዕከል እና የተለያዩ ማዕከላት ግንባታ የሚደነቅ ሆኖ መመልከታቸውን በመርሐ ግበሩ እየተሳተፉ የሚገኙት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አረጋ ከበደ ተናግረዋል፡፡

ለዚህ ስኬት የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ቁርጠኝነትን የተመለከቱበት መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

የኑሮ ውድነትን ለመቀነስና ዘመናዊ የንግድ ስርዓትን ለመፍጠር በከተማዋ የተገነቡ ዘመናዊ የንግድ ማዕከላትን ጨምሮ እየተካሄዱ ያሉ የግብርና ስራዎች የዜጎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ናቸውም ብለዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ እየተተገበሩ የሚገኙ የተለያዩ ልምዶችን በመውሰድ ክልላቸውን ለማልማት እየሰሩ መሆናቸውንም ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል፡፡

በሩዝሊን መሃመድ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review